Skip to the content
The Maryland-National Capital Park and Planning Commission
Home / News / ለፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኒ ማስተር ፕላን አራት ተከታታይ ምናባዊ መንገድ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ህብረተሰቡ እንዲሳተፉ እና ግብረመልስ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል

ለፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኒ ማስተር ፕላን አራት ተከታታይ ምናባዊ መንገድ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ህብረተሰቡ እንዲሳተፉ እና ግብረመልስ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል

fairland-briggs-chaney-logo
የመከሩ ተከታታይ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜ በፓርኮች እና መዝናኛዎች፣ ዘላቂ እድገት እና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ መጓጓዣ እና እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም ፍትሃዊ የምግብ ስርዓቶች ላይ ያተኩራል

WHEATON MDየሞንትጎሜሪ ካውንቲ ዕቅድ መምሪያ፣ የሜሪላንድ-ብሔራዊ ካፒታል ፓርክ እና ዕቅድ ኮሚሽን (M-NCPPC) ክፍልበፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኒ ማስተር ፕላን ላይ ማህበረሰቡ በአራት ተከታታይ ምናባዊ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜ ላይ እንዲገኝ ጋብዟል ተከታታይ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎቹ በፓርኮች እና በመዝናኛ፣ በዘላቂ እድገት እና በኢኮኖሚ ልማት፣ በትራንስፖርት እና በእንቅስቃሴ እና በፍትሀዊ የምግብ ስርዓቶች ላይ ያተኩራሉ። እያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜዎች ነፃ ሲሆኑ በማይክሮሶፍት ቡድኖች መድረክ በኩል በእውናዊ መንገድ በመስመር ላይ ይስተናገዳሉ እንዲሁም ተቀድተው ይቀመጡ እና በተፈለጉ ጊዜ እንዲገኙ ይደረጋል። RSVPዎች ቢያንስ በ 10 የሥራ ቀናት ማሳወቂያ በኩል በ RSVP ቅጽ (ከዚህ በታች ባሉት አገናኞችን ይግቡ) ሲጠየቁ ከትርጉም አገልግሎቶች ጋር እንዲሆኑ ይፈለጋል። ተከታታይ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜው ዓላማ የማስተር ፕላኑ ሂደት ማህበረሰቡን የማሳተፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ እያለ የማህበረሰብ አባላት እና ባለድርሻ አካላት ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ እና የሞንትጎሜሪ ፕላን ሰራተኞችን ጥያቄዎች እንዲጠይቁ ዕድል መስጠት ነው።

እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ በሞንትጎመሪ ፕላን ሠራተኞች የሚመራ ሲሆን ስለ ማስተር ፕላኑ ዳራ አጭር አቀራረብን የሚያካትት ይሆናል፣ በመቀጠልም ተሳታፊዎች ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች እና ለወደፊቱ ያሏቸውን ግቦች የሚያጋሩበትን የማዳመጥ ክፍልን ያካትታል። ውይይቶቻችንን ለማነቃቃት እና ግንዛቤን ለመጨመር፣ ዝግጅቶቹ በማነሳሳት፣ በማነቃቃት እና ለተሳትፎ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮችን በማፍረስ ችሎታቸው የሚታወቁትን የታሪክ መጣጥፎችን ያካትታሉ።

የዝግጅቱ ዝርዝሮች፦

መናፈሻዎች፣ መዝናኛዎች እና የመጫወቻ ቦታዎች
ሰኞ ኖቬምበር 1፣ 2021፥ 6:30 p.m. እስከ 8:00 p.m.
RSVP

ፍትሃዊ ማህበረሰብ፣ ንቁ ኢኮኖሚ እና ጤናማ አካባቢ
ሃሙስ ኖቬምበር 4፣ 2021፥ 6:30 p.m. እስከ 8:00 p.m.
RSVP

ተንቀሳቃሽነት እና ፍትሀዊ መሠረተ ልማት
እሮብ ኖቬምበር 10፣ 2021፥ 6:30 p.m. እስከ 8:00 p.m.
RSVP

ምግብ ለእድገት
አርብ ኖቬምበር 19፣ 2021፥ 10:00 a.m. እስከ 11:30 a.m.
RSVP

ተከታታይ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜው ለካውንቲው አጠቃላይ ዕቅድ ዝመና በ እድገት ሞርትጎሜሪ 2050 የዕቅድ ሰሌዳ ረቂቅ ውስጥ ባለው ለመሠረት አስፈላጊ የሆነውን የተሟሉ ማህበረሰቦችን ጽንሰ-ሀሳብ ያብራራሉ። የተሟሉ ማህበረሰቦች የዘር እና የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለመደገፍ የተለያዩ የቤተሰብ ዓይነቶችን፣ የገቢ ደረጃዎችን እና ተመራጭ የሆኑ ነገሮችን ጨምሮ የተለያዩ የመሬት አጠቃቀሞችን፣ አገልግሎቶችን እና መገልገያዎችን የሚያካትት የእቅድ መርህ ነው።

የእቅድ አውጪ ዳይሬክተር ግዌን ራይት “ስለ ፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኔይ ወደፊት ላይ ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው በዚህ መኸር ተከታታይ እውናዊ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎች ላይ እንዲገኝ እጋብዛለሁ” ብለዋል። “በማህበረሰብዎ ውስጥ ወደፊት ምን ሊመስል እንደሚችል አስተያየት መስጠት፣ ማዳመጥ እና ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላሉ። በዚህ የማስተር ፕላኑ ሂደት ወቅት የምናገኘው ግብረመልስ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ለዚህ አስፈላጊ የሞንትጎሜሪ ካውንቲ ማኅበረሰባችን እድሎችን ሊሰጡ የሚችሉ ምክሮችን ለማሳወቅ ይረዳል።”

ስለ ፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኔ ተከታታይ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎች

መናፈሻዎች፣ መዝናኛዎች እና የሚጫወቻ ቦታዎች
ሰኞ ኖቬምበር 1 2021 6:30 p.m. እስከ 8:00 p.m.

ተደራሽ እና በፍትሃዊ መንገድ የተከፋፈሉ ፓርኮች እና መዝናኛዎች ለተሟሉ ማህበረሰቦች ዋና ነገሮች ናቸው። መናፈሻዎች፣ መራመጃዎች፣ እና ክፍት ቦታ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን የሚያበረታቱ፣ ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚፈጥሩ፣ እና አዕምሮን የሚያጎሉ እና መንፈስን የሚያድሱ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎችን የምናጣጥምባቸው ናቸው። ፓርኮች እና ሌሎች የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ማህበራዊ ትስስርን እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ስትራቴጂዎችን በመገንባት ላይ ወሳኝ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ የ ሞርትጎሜሪ እቅድ አውጪ ሠራተኞች ነዋሪዎችን እና ባለድርሻ አካላትን በማዳመጥ ከፓርኮች እና ከመዝናኛ ቦታዎች ጋር ስላላቸው ልምምዶች የበለጠ ይማራሉ። ሰራተኞች አሰሪዎችን እና ተቀጣሪዎችን ለመሳብ፣ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ለመገንባት እና እንደ አንድ የተሟላ ማህበረሰብ አካል ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎችን ለማበረታታት የሚሆኑ ፓርኮችን፣ መዝናኛዎችን እና የህዝብ ቦታዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማቀናጀት ግብአቶችን ይፈልጋሉ።

ፍትሃዊ ማህበረሰብ፣ ንቁ ኢኮኖሚ እና ጤናማ አከባቢ
ሐሙስ ኖቬምበር 4 2021 6:30 p.m. እስከ 8:00 p.m.

የተሟሉ ማህበረሰቦች የዘር እና የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለመደገፍ የተለያዩ የቤተሰብ ዓይነቶችን፣ የገቢ ደረጃዎችን እና ተመራጭ የሆኑ ነገሮችን ጨምሮ የተለያዩ የመሬት አጠቃቀሞችን፣ አገልግሎቶችን እና መገልገያዎችን የሚያካትት የእቅድ መርህ ነው። ተዛማጅ የሆነው የ “15 ደቂቃ መኖር” ጽንሰ-ሀሳብ፥ በአካባቢያቸው በእግር ጉዞ ርቀት ውስጥ የሰዎችን የዕለት ተዕለት ፍላጎቶች የሚያሟሉ ሥራዎችን፣ አገልግሎቶችን፣ መሠረተ ልማቶችን፣ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን እና መገልገያዎችን መገመቻ መንገድ ነው። እነዚህ ጽንሰ-ሀሳቦች የአካባቢያችንን ኢኮኖሚ ለማራቀቅ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ ጤንነትን፣ ፍትሃዊ ማህበረሰቦችን እና አካባቢያዊ የመቋቋም ችሎታ ለማረጋገጥም ጭምር አስፈላጊ ናቸው። በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ የሞንትጎሜሪ እቅድ አውጪ ሠራተኞች ማዳመጥን ይቀጥላሉ እና ተሳታፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በፌርላንድ እና በብሪግስ ቻኔ ውስጥ እንዴት እንደሚኖሩ፣ እንደሚሠሩ፣ እንደሚተሳሰሩ እና እንደሚጫወቱ – እና ለማደግ ምን እንደሚያስፈልጋቸው የበለጠ ይማራሉ።

ተንቀሳቃሽነት እና ተመጣጣኝ መሠረተ ልማት
ረቡዕ፣ ኖቬምበር 10 2021 630 p.m. እስከ 800 p.m.

ሰዎችን እና ቦታዎችን ከሥራ፣ ከመገልገያዎች እና ከአገልግሎቶች ጋር የሚያገናኝ ፍትሃዊ የትራንስፖርት ሥርዓት ከሌለ የትኛውም ማህበረሰብ የተሟላ አይደለም። በመተላለፊያ፣ በእግር መጓዣ፣ በማሽከርከሪያ እና በብስክሌት መንጃ መሠረተ ልማት ላይ ለሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ከፍተኛ ቅድሚያ መስጠት የተሟላ እና ፍትሃዊ ማህበረሰብን ለመገንባት ወሳኝ ነው። በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ የሞንትጎሜሪ እቅድ አውጪ ሠራተኞች ነዋሪዎችን እና ባለድርሻ አካላትን ያዳምጣሉ እና ስለ ተንቀሳቃሽነት እና ዘወር ዘወር ስለማለት ልምዶቻቸው የበለጠ ይማራሉ። ፍትሃዊነትን፣ ጥሩ ጤናን እና የህይወት ጥራትን እያስተዋወቁ የበለጠ ተንቀሳቃሽነትን፣ ተደራሽነትን እና ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬን የሚደግፍ አውታረ መረብ እንዴት መገንባት እንደምንችል ግብአቶችን እንፈልጋለን።

ምግብ ለእድገት
ዓርብ፣ ኖቬምበር 19 2021 10:00 a.m. እስከ 11:30 a.m.

የሚያድግ ማህበረሰብ ማደግ፣ መሸጥ እና ጤናማ ምግብ መመገብ ይችላል። ጤናማ ምግብ ትኩስ፣ ገንቢ፣ ተመጣጣኝ፣ ከባህል ጋር የሚስማማ እና በአካባቢው የሚበቅል ነው። የበለጠ በራስ የመተማመን ያለው፣ ጤናማ እና ፍትሃዊ ማህበረሰብን ማሳደግ ይችላል። በዚህ ክፍለ ጊዜ፣ የሞንትጎመሪ ዕቅድ ሠራተኞች አሁን ያሉትን የምግብ ሥርዓቶች፣ የመሬት አጠቃቀም እንቅፋቶች፣ ስለ ተሳታፊዎች ተግዳሮቶች እና ሀሳቦች ይማራሉ፣ እና ለፌርላንድ እና ለብሪግስ ቻኒ የምግብ እኩልነትን ለማሳካት መንገዶች ላይ ይወያያሉ።

ተመጣጣኝ ተሳትፎ

የፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኔ ማስተር ፕላን ዋና ክፍል ነዋሪዎችን፣ የንግድ ባለቤቶችን፣ መሠረታዊ የማህበረሰብ አደራጆችን፣ ባለሙያዎችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን እንዲሁም የካውንቲው የመንግስት ተወካዮችን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ትርጉም ያለው ግብዓት ለመሰብሰብ አጠቃላይ እና ፍትሃዊ ተሳትፎ እና የግንኙነት ዕቅድ ነው። የሞንትጎመሪ ዕቅድ አውጪ እና ማህበረሰቡ አብረው ከተሰበሰቡት ታሪኮች፣ ከአፍ ታሪኮች፣ ከአሁኑ ልምዶች፣ ከካርታ መሳሪያዎች፣ ከትንተናዊ መረጃዎች እና ልምዶች ይማራሉ እንዲሁም እንዲፈጠር የረዱትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሀዊ ወደፊት ያቅዳሉ። በሚቀጥሉት ዓመታት በፌርላንድ እና በብሪግስ ቻኒ ውስጥ ያለው ሕይወት ምን ሊሆን እንደሚችል ከማህበረሰቡ ጋር እንመረምራለን እንዲሁም እንገምታለን።

የመኸሩ የማዳመጥ ክፍለ-ጊዜዎች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ዕቅድ ቦርድ በኤፕሪል 2021 የማስተር ፕላኑን  የሥራ ወሰን ማፅደቅን እና እና በጸደይ 2021 በተካሄደው በፌርላንድ እውናዊ ተናጋሪዎች ተከታታይ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የማህበረሰቡን ውይይቶችን  የሚከተል ነው።

የበለጠ ለመረዳት፦በፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኔ ማስተር ፕላን ድህረ -ገጽ ላይ

ይመዝገቡ፦ለፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኔ ማስተር ፕላን ኢሌተር

ይሳተፉስለ ፌርላንድ እና ብሪግስ ቻኒ በመስመር ላይ ባለ መጠይቅ ላይ

ያናግሩ፡ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች Molline.Jackson@montgomeryplanning.org ወይም Phillip.Estes@montgomeryplanning.org

Fairland እና Briggs Chaney ማስተር ፕላን

የ Fairland እና Briggs Chaney ማስተር ፕላን የ of the 1997 Fairland  ማስተር ፕላን ክፍል የተሻሻለዉ ሲሆን፣ ለ Fairland ማህበረሰብ ፍትሃዊ የሆነና የበለጸገ ነገን የያዘ ግልጽ ሕልም በመመስረት፣ የካውንቲዉን የረጅም ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ እንደንቁ ኢኮኖሚ፣የነዋሪዎች ፍትህ እንዲሁም ጤናማ አካባቢን የያዙ ነገሮችን ማንጸባረቅ። የማስተር ፕላን ወሰኑ የያዘው ዋነኛዉ ነገር የ Fairland እና Briggs Chaney ንብረትና ማህበረሰብ በደቡብ ከ Paint Branch በቅርብ ካለዉከ US 29 ኮሪደር ጋር ወደ Greencastle መንገድ በሰሜን በኩል ነዉ። የተሻሻለዉ የሚመረምረዉና የሚያቀርባቸዉ፣ ባሉትና በሚመጡት የመሬት አጠቃቀሞችና የዞን ክፍፍል ፖሊሲዎችና ምክሮች፣ በትራንስፖርት ሲስተሞች፣ታሪካዊ በሆኑ የማቆያ እድሎች፣የአካባቢ ፓርክ ፋሲሊቲዎችና አካባቢዎች ነዉ። ይህ ማስተር ፕላን ከፍትህ ማዕቀፍ ፍንጮችን ከተሻሻለዉ የካዉንቲዉ አጠቃላይ እቅድ በመዉሰድ Thrive Montgomery 2050 በማለት ለእድሎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ቦታዎች እንዴት ጠንካራና ስኬታማ ማህበረሰብ እንደሚፈጥሩ ነዉ። የ Fairland እና Briggs Chaney ማስተር ፕላን ግብ የሚከተሉትን ያካትታል፡

ሞንትጎመሪ እቅድ፣በ

ሞንትጎመሪ ካዉንቲ ውስጥ የዘር ኢ-ፍትሃዊነት እንዲፈጠርና እንዲቀጥል የእኛ እቅድና ፖሊሲዎች ሚና መጫወታቸዉን አዉቆ ይቀበላል። ባለፉት ጊዜያት፣ኢ-ፍትሃዊነትን መፍትሄ ለመስጠት፣ለማቃለል እና ለማጥፋት እያደረግን መንገዱን ለማሻሻል ቁርጠኖች ነን እንዲሁም ወደፊት ፍትሃዊ የሆኑ ማህበረሰቦችን ለመፍጠር የእቅድ መፍትሄዎችን አዘጋጅተናል።  በእቅድ ማዉጣት ሂደቱ ውስጥ ፍትሃዊነትን ለማስፈን በሚደረገዉ ሙሉ የአካሄድ ግንባታ ጊዜ የሚፈጅ ነገር ቢሆንም፣ በስራችን ላይ የፍትህ መስፈን እንዳየተገበር ማዘግየት አንችልም። እስካሁን ያሉት ጥረቶች የሚያጠቃልሉት፡