Skip navigation

ሶስት ክፍሎች ያሉት ተከታታይ የሆነ ቨርቹዋል ተናጋሪ ፕሮግራም በ Fairland እና Briggs Chaney ማስተር ፕላን የሚጀምረዉን እንዲሳተፍ ማህበረሰቡ ተጋብዘዋል።

May 13, 2021

CommUNITY Conversations in Fairland Amharic
“የማህበረሰብ ዉይይቶች በ Fairland” በሜይና በጁን ይከናወናል እንዲሁም ትኩረቱን የሚያደርገዉ በዘር ፍትሃዊነት፣ በህበረተሰባዊ ፍትህ እና የ Route 29 ኮሪደርን እንደገና በማሰብ ነዉ

WHEATON, MD – The Montgomery ካዉንቲ የእቅድ መምሪያ፣የ የሜሪላንድ ብሄራዊ ካፕታል ፓርክና የእቅድ ኮሚሽን (M-NCPPC) ነዋሪዎችን፣የማህበረሰብ አባላትን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ሶስት ክፍል ላለዉ   የማህበረሰብ ዉይይቶች በ Fairland፣ ለFairland እና Briggs Chaney ማስተር ፕላን ዋናዉ ማስጀመሪያ መነሻ ተብሎ ለሚጠራዉ ተከታታይ የቨርቹዋል ተናጋሪ ፕሮግራም ተጋብዘዋል። ተከታታይ ፕሮግራሙ በእቅዱ ዉስጥ ጥናት የሚደረግባቸዉ እንደ የዘር ፍትሃዊነት፣ የማህበረሰብ ግንኙነት፣የእግረኛ ደህንነት፣ፓርኮችና ክፍት ቦታዎች፣ባህላዊ ሀብቶች እና ወዘተ. ያሉትን አጠቃልሎ ቁልፍ ርእሶችን ይሸፍናል። የተከታታይ ፕሮግራም ተናጋሪዉ አራት ክፍሎች ያሉትን የተሳትፎ እቅድ በማጠቃለል የስራዉን ስፋት የሚያጸድቀዉን የእቅድ ቦርድ ይከተላል።

የ Montgomery የእቅድ ዳይሬክተር የሆኑት Gwen Wright እንዲህ አሉ “የ Fairland እና Briggs Chaney ነዋሪዎችን እና የቢዝነስ ባለቤቶችን ስለማህበረሰባቸዉና ከማስተር ፕላን የማዉጣት ሂደቱ ጋር ሊሆን የሚችለዉ ምን እንደሆነ ውይይት ማድረግ እንዲጀምሩ እንኳን ደህና መጣችሁ ስል በጣም በደስታ ነዉ”። “ሁሉም ሰዉ እንዲሳተፍ ተጋብዘዋል እንዲሁም የዚህን ጠቃሚ የእቅድ ሂደት መስሚያ ደረጃ ስንጀምር፣ የሁሉንም ሰው ድምጽ መስማት እንፈልጋለን።”

እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ፕረዘንቴሽን እንዲሁም ጥያቄና መልስ/ አጭር አስተያየት ጊዜ እንዲኖረዉ ተደርጎ ተዘጋጅቷል። መርሃ ግብሮቹ ተቀርጸዉ በ Fairland እና Briggs Chaney ፕሮጀክት ገጽ ላይ በኦንላይን ይለቀቃሉ።  የተናጋሪ ተከታታይ ፕሮግራሙ ለመሳተፍ ነጻ ሲሆን በማይክሮሶፍት ቴሌኮንፈረንሲንግ አገልግሎቶች በቨርቹዋል ይቀርባል። RSVP ያደረጉት ስብሰባዉን እንዲታደሙ ያስፈልጋል።

ክፍለጊዜያት:

በተቀደሰዉ መሬት አዳዲስ ግኝቶች በአካባቢዉ ላዉ ፈር ቀዳጆች ክብር መስጠት – ሜይ 18 (6 – 8 p.m.)

ከአምስት አመት በፊት የአፍሪካ አሜሪካዊያን የታሪክ ቦታዎች ከተከፈቱ በኋላ የታሪካዊ ማቆያ ክፍሉ የካዉንቲዉን ሙሉ ታሪክና ቅርስ በታማኝነትና በፍትሃዊነት ለማቅረብ ቃል ገብቷል። የአፍሪካ አሜሪካዊያን የቅርስ ስፍራዎችን ግንዛቤ ለማስፋት እያደረግን ባለዉ ጥረቶች(እንደ የመቃብር ስፍራዎች፣ቤተክርስቲያኖች፣ የገበሬ ቤቶችና የግብርና ቦታዎች ያሉ) እንዲሁም  በማህበረሰብ አባላት መካከል  ንግግር እንዲካሄድ እያበረታታን፣ በ Fairland አካባቢ ጉልህ ሰዎች የነበሩትን ሁለቱንም Sarah Lee እና Malinda Jackson አሻራን የሚገልጽ ዘጋቢ ፊልም ታዳሚዎች ይመለከታሉ። ዘጋቢ ፊልሙ ታሪካቸዉን ከተለያዩ እይታዎች አንጻር ይተርከዋል። ከዘጋቢ ፊልሙ ቀጥሎ ፓናሊስቶች የጥያቄና መልስ ክፍለ ጊዜ ያደርጋሉ። ምዝገባ ያስፈልጋል እንዲሁም ይህ ፕሮግራም ለ AICP እና ASLA ተከታታይ የትምህርት ክሬዲቶች ጸድቋል።

የመክፈቻ አስተያየቶች፡
Tanya Stern፣ የ Montgomery ካውንቲ የእቅድ ክፍል ምክትል ዳይሬክተር

አወያይ፡
Molline Jackson (ለ Fairland እና Briggs Chaney ማስተር ፕላን የጋራ መሪ እቅድ አዉጪ)

ፓናሊስቶች፡
ለ Montgomery ካውንቲ የእቅድ ክፍል አርኪዮሎጂስት Brian Crane፣
ባለቅኔ CeLillianne Green፣ አከናዋኝ አርቲስት
Jamie Ferguson፣ ለ Montgomery ካዉንቲ የፓርኮች ክፍል ሲኒየር ባለታሪክ
Ella LaGrange፣ የተማሪ ተመራማሪዉ
Michael Withers፣ የፕሮፌሽናል አርኪዮሎጂስት Sarah Lee
Varna Boyd የልጅ ልጅ ልጅ ልጅ

የሰዎች ጥቅም-የመጀመሪያ የትራንስፖርት እቅድ – ሜይ 25 (6 – 8 p.m.)

በ Montgomery ካዉንቲ በኮሪደሮቻችን ያሉትን ግንኙነቶችና ማህበረሰቦችን ለማጠናከር፣የትራንስፖርት እቅዱ በዘር ፍትሃዊነትና በህብረተሰባዊ ፍትህ ላይ የሚያሳድረዉን ከግምት ዉስጥ ማስገባት ይኖርብናል። ሁለተኛዉ ክፍለ ጊዜ የእቅድ አካባቢዉ የግንኙነትና የእግረኛ ደህንነት ተግዳሮቶች ላይ ያተኩራል። ክፍለ ጊዜዉ የቪዥኝ ዜሮ መነሻዎችን ስር፣ የእግረኛ ማስተር ፕላን በጥልቀት ይገባል እንዲሁም ከእነዚህ እቅዶች በመነሳት የቅርብ ጊዜ መረጃ ያቀርባል። በ Fairland እና Briggs Chaney ማሀበረሰብ ዉስጥ ያለዉን የእግር ጉዞ ባህልና የእግረኞችን ልምድ በማጣቀስ፣ ታዳሚዎች ከጎረቤት አሸናፊዎች ግላዊ የሆኑ ታሪኮችን ይሰማሉ። ምዝገባ ያስፈልጋል እንዲሁም ይህ ፕሮግራም ለ AICP እና ASLA ተከታታይ የትምህርት ክሬዲቶች ጸድቋል።

አወያይ፡
የ Montgomery ካውንቲ የእቅድ ክፍል ሲኒየር የትራንስፖርት ዳይሬክተር Lauren Campbell

ፓናሊስቶች፡
የ Alan M. Voorhees ትራንስፖርት ማእከል ሲኒየር ተመራማሪ Charles Brown፣
የ Montgomery ካዉንቲ የእቅድ ክፍል የትራንስፖርት እቅድ አዉጪ Jesse Cohn McGowan፣
የ Independent Living Services for Independence Now ዳይሬክተር Shannon Minnick፣
የ Independence Now ተወካይ – በ Prince George ካዉንቲ የ Independent Living ስፔሻሊስት Rochelle Harrod

በማህበረሰብ የአረንጓዴ ቦታ የ Grassroots ተሟጋች:  የማህበረሰብ አስተዋጽኦ ጥበብን በደንብ ማወቅ – ጁን 1 (6 – 8 p.m.)

በFairland እና Briggs Chaney የማስተር ፕላን አካባቢ እንዲሁም በክልሉ ሁሉ፣ፓርኮችና የማህበረሰብ አረንጓዴ ስፍራዎች በከፍተኛ ደረጃ ይፈለጋሉ። ከጎረቤት ሻምፒዮኖች ጋር በመተባበር፣ ይህ ክፍለ ጊዜ በማህበረሰብ ተሳትፎ ስትራቴጂዎች፣በ grassroots ተሟጋችነት፣ የማህበረሰብ አረንጓዴ ስፍራዎች የማግኘት ጭማሪዎች እንዲሁም የምግብ ኔትወርኮች ላይ ያተኩራል። በክፍለ ጊዜዉ ወቅት፣ የማህበረሰብ የአትክልት ስፍራ ፕሮግራም (በ Fairland እና Briggs Chaney አካባቢ) ማህበረሰብንና የስራ ትስስርን ለማጠናከር እድል ከሚሰጡ ፕሮግራሞች አንዱ እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።  ምዝገባ ያስፈልጋል እንዲሁም ይህ ፕሮግራም ለ AICP እና ASLA ተከታታይ የትምህርት ክሬዲቶች ጸድቋል።

የመክፈቻ አስተያየቶችና አወያይ፡
የ Montgomery ካዉንቲ የእቅድ ቦርድ ኮሚሽነር Tina Patterson

ፓናሊስቶች፡
የ Unity Thunder
Heather Bruskin ፕሬዚዳንት Julian McElveen፣የ Montgomery ካዉንቲ የምግብ ካዉንስል
Vanessa Pierre፣የHomestead Hustle & Healing
ዋና ዳይሬክተር Elijah Wheeler፣የMontgomery ካዉንቲ የትብብር ካዉንስል ዋና ዳይሬክተር
Agar Mbianda፣በ Manna የምግብ ማእከል የማህበረሰብ ተሳትፎ ሃላፊ
የማህበረሰብ ጋርደንስ ፕሮግራም ከ ፓርክስ ክፍል ጋር(M-NCPPC) Michelle Nelson፣
የፕሮግራም ሃላፊ II Danielle Alvarado: የምስራቅ ካዉንቲ የክልል ማእከል

ስለ Fairland እና Briggs Chaney ማስተር ፕላን

የ Fairland እና Briggs Chaney ማስተር ፕላን የ of the 1997 Fairland  ማስተር ፕላን ክፍል የተሻሻለዉ ሲሆን፣ ለ Fairland ማህበረሰብ ፍትሃዊ የሆነና የበለጸገ ነገን የያዘ ግልጽ ሕልም በመመስረት፣የካውንቲዉን የረጅም ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ እንደንቁ አኢኮኖሚ፣የነዋሪዎች ፍትህ እንዲሁም ጤናማ አካባቢን የያዙ ነገሮችን ማንጸባረቅ። የማስተር ፕላን ወሰኑ የያዘው ዋነኛዉ ነገር የ Fairland እና Briggs Chaney ንብረትና ማህበረሰብ በደቡብ ከ Paint Branch በቅርብ ካለዉከ US 29 ኮሪደር ጋር ወደ Greencastle መንገድ በሰሜን በኩል ነዉ። የተሻሻለዉ የሚመረምረዉና የሚያቀርባቸዉ፣ ባሉትና በሚመጡት የመሬት አጠቃቀሞችና የዞን ክፍፍል ፖሊሲዎችና ምክሮች፣በትራንስፖርት ሲስተሞች፣ታሪካዊ በሆኑ የማቆያ እድሎች፣የአካባቢ ፓርክ ፋሲሊቲዎችና አካባቢዎች ነዉ። ይህ ማስተር ፕላን ከፍትህ ማዕቀፍ ፍንጮችን ከተሻሻለዉ የካዉንቲዉ አጠቃላይ እቅድ በመዉሰድ Thrive Montgomery 2050 በማለት ለእድሎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ቦታዎች እንዴት ጠንካራና ስኬታማ ማህበረሰብ እንደሚፈጥሩ ነዉ።

ስለፍትሃዊ የሆነ አጀንዳ እቅድ

Montgomery እቅድ፣በ Montgomery ካዉንቲ ውስጥ የዘር ኢ-ፍትሃዊነት እንዲፈጠርና እንዲቀጥል የእኛ እቅድና ፖሊሲዎች ሚና መጫወታቸዉን አዉቆ ይቀበላል። ባለፉት ጊዜያት፣ኢ-ፍትሃዊነትን መፍትሄ ለመስጠት፣ለማቃለል እና ለማጥፋት እያደረግን መንገዱን ለማሻሻል ቁርጠኖች ነን እንዲሁም ወደፊት ፍትሃዊ የሆኑ ማህበረሰቦችን ለመፍጠር የእቅድ መፍትሄዎችን አዘጋጅተናል።  በእቅድ ማዉጣት ሂደቱ ውስጥ ፍትሃዊነትን ለማስፈን በሚደረገዉ ሙሉ የአካሄድ ግንባታ ጊዜ የሚፈጅ ነገር ቢሆንም፣ በስራችን ላይ የፍትህ መስፈን እንዳየተገበር ማዘግየት አንችልም። እስካሁን ያሉት ጥረቶች የሚያጠቃልሉት፡

  • ለእቅድ የፍትሃዊነት አጀንዳን ማዘጋጀት። የእቅድ ቦርዱ  የ ማስተር ፕላኒንግ ማእቀፍ ፍትሃዊነት እንዲኖር አጽድቋል፣እንዲሁም ሰራተኞች በተግባራዊ ነገሮች ላይ እየሰሩ ነዉ።
  • ፍትሃዊነት ተኮር ትንተና። Montgomery እቅድ ተለይቷል እንዲሁም የካዉንቲው የፍትሃዊነት ተኮር አካባቢዎች ተተንትነዋል እንዲሁም የማፒንግ መሳሪያ በማዘጋጀት  የእቅድ ጥረቶች በ Montgomery ካዉንቲ እንዲያብቡና ለማህበረሰቡ በይበልጥ ፍትሃዊ የሆኑ ዉጤቶችን እንዲያስመዘግቡ ነዉ።
  • በ Thrive Montgomery 2050 ፍትሃዊነትን ማስቀደም። የማህበረሰብ ፍትሃዊነት በእኛ የካዉንቲ ዋና እቅድ መሻሻል ላይ ከሶስቱ ቅድሚያ ከሚሰጣቸዉ ነገሮች አንዱ የሆነዉ Thrive Montgomery 2050 ነዉ።
  • ፍትሃዊነት ላይ በሚመጡት እቅዶች ማተኮር።  ፍትሃዊነት የ Silver Spring Downtown እና Adjacent ማህበረሰብ እቅድ ዋናዉ ትኩረት የሆነና የ Montgomery ካዉንቲ የዘር ፍትሃዊነትና የህበረተሰባዊ የፍትህ አክት ከጸደቀበት ጊዜ ጀምሮ ያለ የመጀመሪያው ማስተር ፕላን ነዉ። የሚመጡት ሁሉም እቅዶችና ጥናቶች ፍትሃዊነት ላይ ያተኩራሉ።
  • የአስተዳደርና የኦፕሬሽን ስራዎችን በፍትህ መነጽር ማየት።  ጥረቶቻችን ከማስተር ፕላኒንግ ሂደት ጋር ብቻ የተወሰኑ አይደሉም። እንደኮሚኒኬሽንና የሰዉ ሃይል ያሉ የአስተዳደርና የኦፕሬሽን ስራዎች ሁሉንም ነገር በፍትህ መነጽር እንድናይ የሚያረጋግጡልን ታዳጊ አቀራረቦች፣መሳሪያዎች፣እቅዶች እንዲሁም ስልጠናዎች ናቸዉ።